Fana: At a Speed of Life!

ኢንተርፕራይዞች የዲጂታል ፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ እየተሠራ ነው- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዲጂታል ፋይናንስ አቅርቦት የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የመካከለኛ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከፋይናንስ ተቋማት የሚፈልጉትን ብድር በዲጂታል አማራጮች ማግኘት በሚችሉበት እና የፖሊሲ ጉዳዮችን የሚዳስስ ዐውደ ጥናት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በአውደ ጥናቱ÷ የብድር ማስያዣ ችግሮች፣ አነስተኛ ተቋማት ከአበዳሪ ተቋማት ጋር ያላቸው ግንኙነት ደካማ መሆን እና ያልተሟላ የብድር ታሪክ እና የሂሳብ መዝገብ አያያዝ የመካከለኛና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የገንዘብ አቅርቦት ችግር እንደፈጠረባቸው ተነስቷል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ እንደገለጹት÷ መንግሥት የዲጂታል ፋይናንስ አቅርቦትን ሊያሳልጡ የሚችሉ የዲጂታል መታወቂያ፣ የአዕምሯዊ ንብረት መተመኛ ስርዓት እና የብድር መረጃ ማጣቀሻ ስርዓቶችን የመገንባት ሥራ እያከናወነ ነው፡፡

በብሔራዊ ባንክ ሐሳብን መሰረት አድርገው ስለማበደር የወጡ መመሪያዎች፣ የንግድ ባንኮች የጀመሩት ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች እና የፈጠራ ሐሳብ ላላቸው ሥራ ፈጣሪዎች እየተመቻቹ ያሉ ልዩ የብድር ስርዓቶች፣ እንደ “ምቹ” እና “ቴሌብር” የመሳሰሉ የዲጂታል ብድር አገልግሎቶች ወደ ገበያ መግባት መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል፡፡

ለአገልግሎት ቅልጥፍና እና ለተደረጀ መረጃ አያያዝ ሲባል አበዳሪ ተቋማት አሰራራቸውን ዲጂታል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.