Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በጋምቤላ ክልል በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው መድኃኒት፣ አልባሳትና ተጨማሪ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ተስፋሁን ጎበዛይ ድጋፉን ዛሬ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አስረክበዋል።

አቶ ተስፋሁን በድጋፍ እርክክቡ ወቅት እንደገለጹት÷ ድጋፉ የተደረገው በክልሉ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ነው ።

ድጋፉም መድኃኒት፣ አልባሳት፣ የመጠለያ ፕላስቲክ፣ የቤት ውስጥ መገልገያና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በክልሉ በዘንድሮ ክረምት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከ187 ሺህ በላይ ሕዝብ መፈናቀሉን ጠቁመው÷ ችግሩ ከአቅም በላይ በመሆኑ ሌሎች ድርጅቶችም ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.