አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በዚምባብዌ ፕሬዚዳንት በዓለ ሲመት ላይ ታደሙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በድጋሚ የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሆነው በተመረጡት ኤመርሰን ምናንጋግዋ በዓለ ሲመት ላይ ታድመዋል።
አፈ ጉባኤ አገኘሁ ÷ በፕሬዚዳንቱ ቀጣይ የሥራ ዘመን የሁለቱን ሀገራት ዘመናት የተሻገረ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንት ምናንጋግዋ በፈረንጆቹ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር በተደረገው ምርጫ ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡