Fana: At a Speed of Life!

ከ996 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት እንዲመለስ ተደርጓል – የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  በግማሽ በጀት ዓመቱ ከ996 ሚሊየን ብር በላይና ከ24 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለመንግስት ተመላሽ እንዲሆን መደረጉን የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ባለፉት 6 ወራት ከክልል ኮሚሽኖች ጋር በተሰራው ስራ ከ462 ሚሊየን 157 ሺህ 600 በላይ በጥሬ ገንዘብ በምርመራና ክስ እንዲሁም ከ522 ሚሊየን 631 ሺህ 100 በላይ ብር በተደረገ የአስቸኳይ ጥናትና በአስተዳደራዊ መንገድ ነው ከዝርፊያ ማዳን እና ማስመለስ የተቻለው፡፡
እንዲሁም ከ9 ሚሊየን 844 ሺህ 400 ብር በላይ ገንዘብ ከቅጣት የተገኘ ሲሆን በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች በህገ ወጥ መንገድ የተወረረ ከ24 ሺህ 570 ሄክታር በላይ መሬት ለመንግስት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም 18 የቀበሌ ቤቶች፣ ለእርዳታ የመጣ 274 ኩንታል እህል ከሙሰኞች የማስመለስ ስራ መሰራቱን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.