Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የጊፋታ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የጊፋታ በዓል የወላይታ ብሔር የባህል የቋንቋና የታሪክ ሲምፖዚየም በማካሄድ ነው በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከበረ የሚገኘው፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ እና የባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ገቡ የጊፋታን በዓል በዓለም ቅርስነት ማስመዝገብ ቀዳሚ ጉዳይ ሆኖ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ጊፋታ ፀሎት የሚደረግበት በዓል እንደመሆኑ በሃይማኖት አባቶችና በሃገር ሽማግሌዎች ለሃገር እና በጦር ግምባር ለተሰው ወገኖች የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡

በጊፋታ በዓል ታሪካዊ ዳራና አሁናዊ ሁኔታ ያተኮረ ጥናታዊ ፅሁፍ እየቀረበ ሲሆን÷ ሰፊ ውይይት ይደረግበታል፡፡

በበዓሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶን ጨምሮ የተለያዩ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በጥላሁን ሁሴን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.