ለምርጫውና ለህዝበ ውሳኔው በስኬት መጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል – የምዕራብ ኦሞ ዞን
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18 ፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ለሚደረገው ምርጫና የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን በደቡብ ክልል የምዕራብ ኦሞ ዞን ምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡
ዞኑ በፀጥታና በሌሎች ምክንያቶች 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ከተራዘመባቸው አንዱ ሲሆን÷ በምርጫ ቦርድ ውሳኔ መስከረም 20 ቀን ይከናወናል፡፡
በተጓዳኝ የደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ህዝበ ውሳኔ በዕለቱ የሚከናወን ሲሆን÷ ለዚህም አስፈላጊው ቁሳቁስ ወደ የምርጫ ማዕከላት ተሰራጭቶ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የጽሀፈት ቤቱ ሃላፊ ወይዘሪት ዮርዳኖስ ሸለመው ገልጸዋል፡፡
በተጎዳኝነት የሚደረገው ምርጫ እና ህዝበ ውሳኔ በስኬት ይጠናቀቅ ዘንድ በፀጥታ ረገድም አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር አሸናፊ ቸርዋል ተናግረዋል፡፡
የዞኑ ፖሊስ አባላት፣ ህዝባዊ ሚሊሻዎች እንዲሁም የክልል ልዩ ሃይል አባላት አስፈላጊ ዝግጅት ማድረጋቸውንም አብራርተዋል፡፡
በደቡብ ክልል ምዕራብ አምስት ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ በክልልነት ለመደራጀት አልያም በቀደመው ደቡብ ክልል ለመቀጠል በህዝብ ድምጽ ይሰጣል፡፡
በአደም አሊ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!