በመዲናዋ የህወሓት እና ሸኔን ተልዕኮ ሊያስፈጽሙ የነበሩ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሽብር ቡድኖቹን ህወሓት እና ሸኔ ተልዕኮ ሊያስፈጽሙ የነበሩ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቁ።
በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሃሰን ነጋሽ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም በአዲስ አበባ አሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ ሊያስፈጹሙት የነበረው የጥፋት ሴራ መክሸፉን ነው የገለጹት፡፡
በዚህ መሰረትም የሽብር ቡድኖቹን ህወሓት እና ሸኔ ተልዕኮ ሊያስፈሙ የነበሩ በርካታ ግለሰቦች እና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡
በሃገሪቱ ዋና ከተሞች የተለያዩ ሁከትና የሽብር አመጽ በማነሳሳት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደርገው ጥረት ከሽፏል ተብሏል።
በተለይም በቤኒሻንጉልና ጋምቤላ የአሸባሪውን ተላላኪዎች እስከ ጦር መሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በጸጋየ ወንደሰን
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!