Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በአሸናፊነት ውስጥ ሆነው የጠላት ሃይሎች እጃቸውን እንዲሰጡ መጠየቃቸው ያላቸውን የሞራል ልዕልና የሚያሳይ ነው – ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸናፊነት እና በድል አድራጊነት ውስጥ ሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ለተሰለፉ ሃይሎች እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ማሳሰባቸው እሳቸውን እና መንግስታቸው ያለውን የሞራል ልዕልና የሚያሳይ ነው አሉ ምሁራን።

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ መሐመድ ሰይድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትግራይ ወጣቶች የቀረበው የሰላም ጥሪ የመንግስትን ሰላም ወዳድነት ያረጋገጠ በአንጻሩ የአሸባሪው ቡድን የቆመበት መሰረት የዜጎችን ደም በማፍሰስ አገርን መዝረፍና ማፍረስ መሆኑን በግልጽ ያሳየ ነው።

የሽብር ቡድኑ በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ሶስት ትውልድ የትግራይ ወጣቶችን በፈጠረው የሃሰት ትርክት ፕሮፖጋንዳ ማስቀጠፉን ያስታውሱት ደግሞ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ሱራፌል ጌታሁን ናቸው።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትግራይ እናቶች የቀረበው ጥሪም የሽብር ቡድኑ ዳግም የትግራይ እናቶችን ዋጋ እንዳያስከፍል እንዲያጤኑ የተሰጠ ዕድል ነው ብለዋል።

አጋጣሚውን ተጠቅመው በርካታ ለሽብር ቡድኑ የተሰለፉ ወጣቶች እጃቸውን እንደሚሰጡ የሚጠበቅ በመሆኑ መቀበል እንደሚገባ የህግ መምህሩ መሐመድ ሰይድ አሳስበዋል።

ሆኖም ግን የመንግስት የሞራል ልዕልና ከፍ ማለት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ከሽብር ቡድኑ ሀሳብ ጋር ተጣብተው የቆሙና በተስፋ መቁረጥ ሊያስከትሉ የሚችሉትን የጥፋት በትር ህዝቡ ተደራጅቶ መመከት እንደሚገባው የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ሱራፌል ጌታሁን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የሽብር ቡድኑ ሽንፈት በገጠመው እና ፈርጥጦ በወጣባቸው አካባቢዎች የታየው ሴቶችን የመድፈር፥ ትምህርት ቤቶችን እና የጤና ተቋማትን ማፍረስ እና ዝርፊያ ህብረተሰቡ ለአፍታም መዘንጋት እንደሌለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመሆኑም የሽብር ቡድኑ ንብረት አውድሞ እና ዘርፎ ለመውጣት ጥረት የሚያደርግባቸው አካባቢዎች ህዝቡ በተደረጀ መንገድ በጋራ መከላከል እና ማስቆም እንዳለበትም ምሁራኑ አሳስበዋል።

በበላይ ተስፋዬ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.