የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በኦሮሚያ ክልል ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ተኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ‹‹ወንድማማችነት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ቃል በሸራተን አዲስ ሆቴል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡
በሥነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አብዲ ተገኝተዋል፡፡
የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱራህማን እንደገለጹት÷ የዘንድሮውን በዓል ለየት የሚያደርገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር ዘምተው አመራር እየሰጡ ባሉበትና እሳቸውን በመከተል የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአንድነት በመነሳት የውጭና የውስጥ ጠላቶችን በጋራ እየመከቱ ባሉበት ወቅት መከበሩ ነው፡፡
የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት “ወንድማማችነት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ይተወቃል ።
የፊታችን ህዳር 29 በአገር አቀፍ ደረጃ በድሬራዋ ከተማ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
በዓሉ ኢትዮጵያ በሽብርተኛው ህወሓትና በውጭ ኃይሎች ሴራ የህልውና ፈተና ላይ ባለችበትና ድል እያስመዘገበች በምትገኝበት በአሁኑ ወቅት ”ወንድማማችነት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል መከበሩ፥ በደም የተሳሰረው የኢትዮጵያን ህዝቦች አንድነት ይበልጥ የተጠናከረ እንደሚያደርገው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መግለፁ ይታወሳል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!