Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ – ኬንያ ወዳጆች ማኅበር ለኢትዮጵያ ያለውን አጋርነት ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኬንያ ወዳጆች ማኅበር ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ህልውና ለማፅናት የሚያደርጉትን ተጋድሎ እንደሚደግፍ ገልጿል።
የማኅበሩ ሊቀመንበር እና የቀድሞ የናይሮቢ ከንቲባ ጆ አኪች ዛሬ ሚሲዮኑ ለተመደቡ አዲስ ዲፕሎማቶች በተዘጋጀ ሥልጠና ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት የአጋርነት መልዕክት በዚህ ፈታኝ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን ልንቆም ይገባል ብለዋል።
የማኅበሩ አመራሮች የኢትዮጵያ እና ኬንያ ዕጣ ፈንታ የተሳሰረ መሆኑንም ጠቅሰው፥ ለዲፕሎማቶቹ የኬንያ የማኅበራዊ እሴቶች እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ገለጻ አድርገዋል።
በተለያዩ የኬንያ እና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የትብብር መስኮች በተለይም የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ከሚሲዮኑ ጋር በቅርበት እንደሚሠሩም ገልጸዋል።
ሥልጠናው ለሦስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በቀጣይ የኢትዮጵያ እና ኬንያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዕድል እና ተግዳሮቶች፣ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ኮሙኒኬሽን፣ የቆንስላ እና ዳያስፖራ ጉዳዮች፣ የአስተዳደር እና ፋይናንስ አሠራሮች እንዲሁም የቡድን ግንባታ እና የለውጥ ቀጣይነት ላይ እንደሚያተኩር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.