Fana: At a Speed of Life!

ከህወሓት ወራሪ ኃይል ነፃ በመውጣታቸው መደሰታቸውን የላሊበላ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የላሊበላ ከተማን ለማፍረስ ከመጣውና በጭካኔ ተግባሩ ከሚረካው ከህወሓት ወራሪ ኃይል ነፃ በመውጣታቸው መደሰታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
በአሸባሪው ህወሓት ከተፈጸመባቸው የግፍ ወረራ ነጻ የወጡት ነዋሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት በችግሩ ይበልጥ መተዛዘንን፣ መረዳዳትንና አብሮነትን መማራቸውን ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ እንዳሉት አሸባሪው ህወሓት ከተማቸውን ሊያወድም የመጣ እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው ነው፡፡
የሽብር ቡድኑ በከተማዋ በቆየባቸው ጊዜያት መልከ ብዙ ሰቆቃ ያደረሰባቸው ከመሆኑም በላይ በላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዝርፊያና ውድመት ማድረሱን ገልጸዋል።
“የአሸባሪው ህወሓት ግፍና በደል የሚረሳ ባይሆንም መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይሉ፣ ሚሊሻ፣ ፋኖና ህዝባዊ ሠራዊቱ ከዚህ አረመኔያዊ ቡድን ነጻ ስላወጡን ተደስተናል” ነው ያሉት።
አካባቢያቸው አሁን ከወራሪው ሀይል ነጻ በመሆኑ ከስቃይና ከጭቆና ቀንበር መላቀቃቸውንም ነው የተናገሩት።
“አሸባሪው ህወሓት የሰው ልጅ በዚህ ዘመን ይሰራዋል ተብሎ የማይጠበቅ ግፍ በንፁሀን ላይ ፈፅሟል” ነው ያሉት ነዋሪዎቹ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት።
“ለአራት ወር በቆየበት ላሊበላ ከተማ ጨቅላ ህጻናትና አረጋውያን ሳይቀሩ ገድሏል፤ የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያንም አውድማል፤ ንብረት ዘርፏል።” ብለዋል
“ጥፋት ግብሩ በመሆነው በእዚህ አሸባሪ ቡድን ተሰቃይተናል፤ መከራና እንግልትም ደርሶብናል” ሲሉም አክለዋል፡፡
የቅዱስ ላሊበላ ደብር አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ጽዬስላሴ መዝገቡ በበኩላቸው በጦርነቱ ምክንያት አገልግሎት መስጫ ተቋማት በመውደማቸው ህብረተሰቡ ለከፍተኛ ችግር መዳረጉን ተናግረዋል።
አስተዳዳሪው እንዳሉት ወላድ እናቶች በሕክምና እጦት ህይወታቸው እንዳያልፍ የጤና ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ ቤተ ክርስቲያኗ የበኩሏን እገዛ ብታደርግም የመድሃኒት፣ የነዳጅና የኦክሲጅን እጥረት ተከስቷል።
መንግስት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሥራ እንዲጀምሩ ማድረግና ለህብረተሰቡ የእለት ደራሽ ምግብ በአስቸኳይ በማቅረብ ዜጎችን ከሞትና ከርሃብ እንዲታደግም ጠይቀዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.