ደቡብ ሱዳን በአገሯ ለሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ አደርጋለሁ አለች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በደቡብ ሱዳን ለሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የበለጠ ተቀራረቦ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ።
ውይይቱን ያካሄዱት በደቡብ ሱዳን የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢል ማሃዲ እና የደቡብ ሱዳን የገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ፓትሪክ ኬኔዲ ናቸው።
አምባሳደር ነቢል ደቡብ ሱዳን ከነዳጅ ውጭ ያሉ ገቢዎችን ለማስፋት እያደረገች ያለችው ጥረት አበረታች መሆኑንም ነው የገለጹት።
ዋና ኮሚሽነሩ ዶ/ር ፓትሪክ ኬኔዲ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ኩራት መሆኑን ገልጸው÷ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ለአየር መንገዱ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
አምባሳደር ነቢል ማሃዲ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለኮሚሽነሩ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደቡብ ሱዳን ከሚሰጠው ሰፊ የበረራ አገልግሎት በተጨማሪ፥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጁባ ቅርንጫፍ ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!