Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት የወሎ ዩኒቨርሲቲን አውድሟል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት ትውልድ የሚገነባባቸውን ተቋማት ማውደሙን የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ ገለጹ።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሶስቱም ካምፓሶች በአሸባሪው ህወሓት ሙሉ ለሙሉ ዘረፋና ውድመት ተፈፅሞባቸዋል ብለዋል።

በወሎ ወረራ ፈፅሞባቸው በነበሩ አካባቢዎች እኩይ ተግባር በመፈጸም የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሶስቱንም ካምፓሶች በመዝረፍ እንዳወደማቸው ተናግረዋል።

አሸባሪው ህወሓት የዩኒቨርሲቲውን ደሴ፣ ኮምቦልቻና ጢጣ ካምፓሶችን ሙሉ ለሙሉ ዘርፏል የቀረውንም አውድሟል ነው ያሉት።

በመሆኑም የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩትን ጨምሮ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎችን የሚያስተናግደው ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው ሃይል እንዳልነበር ሆኗል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ።

የዩኒቨርሲቲው ህንፃዎች፣ ዘመናዊ ቤተ ሙከራዎች፣ ቤተ መጻህፍት፣ የኢንተርኔት ሰርቨር እና ሌሎችም ንብረቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንም ገልጸዋል።

አሸባሪው ህወሓት የሲቪል ማህበረሰብና ተቋማትን ኢላማ በማድረግ “በዓለም የጦርነት ታሪክ ያልታየ ጭካኔ የታየበት የጦር ወንጀል ፈፅሟል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.