Fana: At a Speed of Life!

የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ እንቅስቃሴ ተጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ በቻይና ባለሃብቶችና በኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ባለቤትነት እየተገነባ የሚገኘውን የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ እንቅስቃሴ ተጎብኝቷል።

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ተገኝተዋል።

ኢንጅነር ታከለ በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በሁሉም ዘርፍ አገራዊ የምርት አቅማችንን በማሳደግ በሀገራዊ ፍላጎት እና አቅርቦት መካከል መመጣጠን መፍጠር ዋነኛው አላማችን ነው ብለዋል።

ይህን ለማድረግም በየትኛውም አካባቢ የሚገኝ የማዕድን ሀብታችንን ጥቅም ላይ እንዲውል እናደርጋለንም ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፡፡

በአንድ በኩል በምርት ላይ ያሉ አምራች ፋብሪካዎችን በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ በማገዝ ፥ በሌላ በኩል ደግሞ አቅምና የሥራ ፍላጎት ያላቸውን አምራች ኢንዱስትሪዎችን በስፋት ወደ ኢንቨስትመንት በማስገባት እንደሚሳካም አንስተዋል።

የግንባታ እንቅስቃሴው ተጠናቆ በአፋጣኝ ወደ ምርት እንዲገባም ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ከአማራ ክልል ጋር በትብብር እንደሚሰሩም ነው ኢንጂነር ታከለ የገለጹት።

በተጨማሪም በክልሉ ያለውን የማዕድን ምርት በአፋጣኝ ወደ እንቅስቃሴ መመለስም በፍጥነትና በከፍተኛ ትኩረት የሚሰራ ቀጣይ ተግባር እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.