የየካ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪዎቹ የህውሓትና ሸኔ ቡድኖች በፈፀሙት ወረራ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ መጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርገዋል።
የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው በመጠለያ ያሉ ወገኖችን ተዘዋውሮ በመጎብኘት ከሰራተኞች የተሰበሰቡ የአልባሳት፣ የምግብ ግብዓትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አስረክቧል።
የክፍለ ከተማው ሰራተኞች ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እስከሚመለሱ ድረስ ከጎናቸው እንደሚቆሙና ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኮሚቴው አስተባባሪዎች ተናግረዋል።
በዞኑ በሚገኙ መጠለያዎች ከ441 ሺህ 625 በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙና በደብረ ብርሃን ከተማ ደግሞ ከ250 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች መኖራቸው ተገልጿል።
ከእነዚህ ውስጥ 23 ሺህ ያህሉ ከኦሮሚያ ክልል ሸኔ ያፈናቀላቸው መሆናቸውን የደብረ ብርሃን የአደጋና ስጋት መከላከል ቡድን መሪ አቶ ደረጀ ይንገሱ ገልፀዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!