ብቁ እና ተወዳዳሪ የሰው ሀብት በመፍጠር ክልሉን ማዘመን የትምህርት ዘርፉ ዋና ዓላማ ነው- የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የለማ የሰው ሀብት በመፍጠር ክልሉን ማዘመን የትምህርት ዘርፉ ግዴታ እና ተግባር መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማተቤ ታፈረ ገለጹ፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ውይይቱ ̋ የትምህርት ልማት ስራው በአሸባሪው ቡድን አይደናቀፍም”̎ በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በውይይት መድረኩ ክልሉ በአሸባሪው የህውሓት ቡድን በደረሰበት ወረራ የትምህርት ስራውም ተደናቅፎ እንደነበረ ተገልጿል።
አብዛኛው የክልሉ የትምህርት ተቋማት ወደ መማር ማስተማር ስራቸው ተመልሰው እየሰሩ እንደሆነም ተመላክቷል።
የለማ የሰው ሀብት በመፍጠር ክልሉን ማዘመን የትምህርት ዘርፉ ግዴታ እና ተግባር መሆኑን የገለጹት ዶክተር ማተቤ÷ ከምኞት በዘለለ ስኬት ለማግኘት ግን በቆራጥነት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
በክልሉ የጎልማሳ ትምህርትን በመተግበር አርሶ አደሩ ውስጥ ዘመናዊ ለውጥ ተግባራዊ እንዲሆን ሊሰራ ይገባልም ነው ያሉት፡፡
የትምህርት ቢሮው ለዚህ ተግባር ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው ላፊው ያረጋገጡት፡፡
የትምህርት ቤቶችን ቁጥር ማሳደግ የተቋሙ ሃላፊነት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን÷ በጦርነቱ የተጎዱ የትምህር ተቋማትን መልሶ ግንባታ ማከናወን እና ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ይገባልም ተብሏል።
መማር ማስተማሩን ለማሳደግ ግብዓት መሟላትና የፈፃሚ አካላትን አቅምም ማሳደግ በ6 ወሩ የተተኮረባቸው ተግባራት እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!