1 ሺህ 30 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 30 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከተመላሾቹ መካከል 1 ሺህ 26 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ፥ አራቱ ደግሞ እድሜያቸው ከአሥራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉም ተመለካቷል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው 68 ሺህ 657 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡