Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥያቄ የዜጎችን አብሮነት ባከበረ መልኩ እየተፈታ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥያቄዎች የዜጎችን የኖረ አብሮነትና ወዳጅነት ባከበረ መልኩ እየተፈታ ነው ሲሉ የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ።

የሕገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዳይሬክተሩ ዶክተር ኃይለየሱስ ታዬ እና የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አክሊሉ ለማ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የአደረጃጀት ዋነኛው ፋይዳ ዜጎችን በቅርበት ማገልገል መሆኑን  ከግንዛቤ በማስገባትና ስለሀገር ቀጣይነት በማሰብ  የሰከነ ጉዞ ልናደርግ ይገባል ነው ያሉት።

እስካሁንም ለዜጎች የክልል አደረጃጀት በክላስተር መልስ ለመስጠት እየተደረገ ያለው ጥረትም የሚበረታታ መሆኑም ነው ያመላከቱት፡፡

በቀጣይነት መንግስት የታችኛውን መዋቅር  የበለጠ በማጠናከር የዜጎችን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከመፍታት እና ሌሎች ሊነሱ የሚችሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ከመቅረፍ አንጻር የጎላ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

በአፈወርቅ አለሙ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.