Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች  የጎድጎድ እና አዳድሌ ወረዳዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ልዑክ የጎድጎድና አዳድሌ ወረዳዎችን ጎበኘ፡፡

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙበሽር ድባድ ራጌ÷የልዑካን ቡድኑ አባላት በአፍዴር ዞን በጎድጎድና ባሬይ ወረዳዎች እንዲሁም በሸቤሌ ዞን አዳድሌ ወረዳ ሥር የሚገኙ የኣቶ እና የኤልበርዴ ቀበሌዎችን የጸጥታ ሁኔታ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ጉብኝቱ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ድንበር ሰላምና ደህንነትን በማጠናከር እንዲሁም የጸጥታ ሃይሎች በቅርቡ ከአሸባሪው አልሸባብ ጋር ባደረጉት የተቀናጀ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ለተጎናጸፉት ድል ምስጋና ለማቅረብ እና ለማበረታታት ያለመ  ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ጉብኝቱ በዞኖቹ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በትግሉ ወቅት ላደረጉት ተሳትፎ ለማመስገንና በድንበር የሚገኙ የጸጥታ አካላትን ለማበረታታት ያለመ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት  የድንበር ጸጥታ ጉብኝት በቀጣይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን÷ በዚህም የአከባቢውን የፀጥታ ሁኔታን የሚመለከቱ  መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.