Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ በቂርቆስ ክ/ ከተማ የተገነቡ ቤቶችን ለአቅመ ደካማ ወገኖች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጵጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተገነቡ ቤቶችን ለአቅመ ደካማ ወገኖች አስረክቧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክፍለ ከተማው ወረዳ 3 በመከላከያ ኮንስትራክሽን አማካኝነትና በሄይንከን ኢትዮጵያ የተገነቡ ቤቶችን መርቀው ለአቅመ ደካማ ወገኖች ቁልፍ አስረክበዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ሰው ተኮር ዕቅድን ማዕከል በማድረግ በ2014ዓ.ም 8 ሺህ ቤቶችን ከተማ አስተዳደሩ ገንብቶ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች አስረክቧል፡፡

ከበጎ ፈቃደኞችና ከአገር ወዳድና ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ከሚወጡ አካላት ጋር ከተቀናጀን ብዙ መሥራት እንደምንችል የተማርንበት ምዕራፍ ነውም ብለዋል፡፡

በዛሬው ዕለት 952 ቤቶችን ከበጎ ፈቃደኛች ጋር በመቀናጀት ግንባታቸውን አጠናቀን አስረክበናል ያሉት ከንቲባዋ÷ተባባሪ አካላት ከደገፉን ለአገር የደከሙ ወገኖቻችንን መደገፍ እንችላለን ነው ያሉት፡፡

የበለጠ እንድንሰራ የእስካሁኑ የአቅመ ደካማ ወጎኖች ቤት ግንባታ ምሳሌ ሆኖናል ማለታቸውንም ከከተማ አስተዳደሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.