ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ሳምንት የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መርሐ ግብር መሠረት ነው ዩኒቨርሲቲዎቹ ከትናንት ጀምሮ ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ የሚገኙት፡፡
በዚህም መሰረት÷ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረብረሀን ዩኒቨርሲቲ፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፣ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ እና ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው፡፡
በተጨማሪም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣ አምቦ እና መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ዋቸሞ እና የወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞችን በመቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡
በተመሳሳይም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞችን መቀበል ጀምሯል::
ለተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምግብና የሕክምና እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች መዘጋጀታቸውም ተገልጿል፡፡
በአለምሰገድ አሳዬ እና በእታገኝ መኮንን ፦ ተጨማሪ መረጃ ከየዩኒቨርሲቲዎቹ