Fana: At a Speed of Life!

ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመንግሥት እና ከግል መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ ጋዜጠኞች አዲስ አበባን እንደስሟ በአዲስ መንገድ የማነፅ አካል የሆኑ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ጠይባ ሎና እንደገለጹት÷ በተግዳሮቶች ውስጥ በማለፍ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅና እና ለሕዝብ ጥቅም ማዋል ተችሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ፕሮጀክቶችን መጀመር እንጂ በታለመለት ጊዜ እና ሁኔታ አጠናቆ ለሕዝብ ጥቅም ማዋል በእጅጉ አዳጋች ነበር ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ደረጃ የሚያሳድጉና ለሕዝብ የላቀ ጠቀሜታ ያላቸውን ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና ጥራት በፍጥነት እያጠናቀቀ በማስመረቅና ለአገልግሎት ክፍት እያደረገ ነው ማለታቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የዛሬው የጉብኝት ዓላማም ከተማ አስተዳደሩ የሚያከናውቸውን አጠቃላይ ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች ሕዝብ እንዲያውቃቸውና በባለቤትነት እንዲከታተላቸው ማስቻል ነው ብለዋል።

ከተጎበኙት ፕሮጀክቶች መካከል÷ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የታላቁ ቤተመንግሥት የቅርስና የመኪና ማቆሚያ፣ የዘውዲቱ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ፣ የየካ ቁጥር-2 መኪና ማቆሚያ፣ የትራፊክ ማኔጅመንት ማዕከል፣ የኮልፌ የገበያ ማዕከል፣ ዘመናዊ የሕጻናትና የወጣቶች ቲያትር ቤት፣ የአርሶ አደሮች ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ግንባታና ሌሎች ይገኙበታል፡፡

የተጠናቀቁትም ሆነ በግንባታ ላይ ያሉት ፕሮጀክቶች በሙሉ የሀገሪቷን የብልጽግና ጉዞ የሚያሳልጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በአዲሱ ሙሉነህ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.