Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት መታሰቢያ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት መታሰቢያ መርሐ ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተካሂዷል፡፡

መርሐ ግብሩ በቦንጋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ የዋለ ሲሆን ፥ የክልሉ አመራሮች፣ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ፓለቲካና የርዕዮተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተዘራ ወልደማሪያም እንዳሉት ፥ የሰሜን ዕዝ ከጀርባ መወጋቱ የማይረሳ የታሪካችን አካል ነው።

ሁለተኛ ዓመቱ ሲዘከር ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ዕውቅና መስጠትንና የክህደት ተግባር ዳግም እንዳይፈጸም ማስገንዘብን ያለመ ነውም ብለዋል አቶ ተዘራ፡፡

መርሐ ግበሩ ጧፍ በማብራት፣ ደም በመለገስ እንዲሁም ለመከላከያ ሠራዊቱን ለመደገፍ በተዘጋጀው የአጭር የጽሑፍ መልዕክት ቁጥር 6800 ላይ ድጋፍ በማድረግ ታስቦ መዋሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.