Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመው ጥቃት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ በሶማሌ ክልል ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት መታሰቢያ “መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመታሰቢያ መርሐ ግበሩ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተወካይና የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጠይብ አህመድ፣  የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ተወካይና አቶ ፈይሰል ፈሺድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

አቶ ጠይብ አህመድ በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ህይወቱን ገብሮ ለሀገራችን ሉዓላዊነት የከፈለው ዋጋ መቼም አይረሳም።

የሀገራችን ህዝቦች ሰራዊታችን እየከፈለ ያለውን መስዕዋትነት በማየት በልማቱ በመድገም ሀገራችንን በጋራ ማሻገር አለብን ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.