Fana: At a Speed of Life!

በኢንዱስትሪ ለውጥ እና በኢኮኖሚ ብዝሃነት ላይ ያጋራ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት በኢንዱስትሪ ለውጥ እና በኢኮኖሚ ብዝሃነት ላይ በኒጀር ኒያሚ ያጋራ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

ምክክሩ በፈረንጆቹ ህዳር 20 ቀን 2022 የሚካሄደውን የአፍሪካን ኢንደስትሪያላይዜሽን እና የኢኮኖሚ ብዝሃነት የመሪዎች ጉባዔ መሰረት በማድረግ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በውይይቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሃሰን ሙሐመድ እየተሳተፉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የአፍሪካ አንድነት ኮሚሽን ከሚመለከታቸው አጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአፍሪካን ኢንደስትሪላይዜሽን እና የኢኮኖሚ ብዝሃነት የመሪዎች ጉባዔ መሠረታዊ ሃሳብ ÷ሁሉን አቀፍ እና ቀጣይነት ያለው ኢንዱስትሪያላይዜሽን የኢኮኖሚ ብዝሃነት ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የግብርና እሴት ሰንሰለቶችን ማሳደግ የአፍሪካ የወጪ ንግድ ሚዛኑን የጠበቀና በዓመት ወደ 115 ቢሊየን ዶላር የሚገመት የወጪ ንግድ ጥገኝነትን እንደሚቀንስ ተጠቁሟል፡፡

የክልልና አህጉራዊ የአግሪ ቢዝነስ ኢንዱስትሪዎች የእሴት ሰንሰለት መጎልበት፣ የአፍሪካን ሕዝብ ለመመገብና የአህጉሪቱን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.