አቶ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ኤሪክ ሜየር ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ላይ ያተኮረ መሆኑን ባንኩ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አመላክቷል።
የባንኩ ገዥ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በኢትዮጵያ እድገትን ለማፋጠን እና የኢኮኖሚ መረጋጋት እንዲመጣ እየተወጣ ላለው ገንቢ ሚና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።