Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ባለስልጣናትን ጨምሮ በ54 የብሪታንያ ዜጎች ላይ ማዕቀብ ጣለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በ54 የብሪታንያ ባለስልጣናት፣ ጋዜጠኞች እና የሕግ አስከባሪ ተወካዮች ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች፡፡

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ÷ ብሪታኒያ በፀረ- ሩሲያ አካሄዷ በሩሲያውያን ላይ የማይገባ ማዕቀብ መጣሏን ተከትሎ አጸፋዊ ምላሽ ሰጥተናል ብሏል፡፡

በዚሁ መሠረት÷ የብሪታኒያ የባህል፣ የሚዲያ እና ስፖርት ሚኒስትር ሉሲ ፍሬዘር እና የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስትር ዴዔታ አናቤል ጎልዲን ጨምሮ በ54 ብሪታኒያውያን ላይ ማዕቀብ ጥለናል ነው ያለው ሚኒስቴሩ፡፡

የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የብሪታኒያ ዜግነት ያላቸው ዓቃቤ ሕግ ካሪም ካንም÷ “በሩሲያ አመራር ላይ የእስር ማዘዣ በማውጣት” በመሳተፋቸው ማዕቀብ ተጠጥሎባቸዋል ብሏል፡፡

‘’ፕሪቬል ፓርትነርስ’’ የተባለ የግል የብሪታኒያ ወታደራዊ ኩባንያ አመራርም የማዕቀቡ ሰለባ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ከቢ ቢ ሲ፣ ጋርዲያን እና ዴይሊ ቴሌግራፍ የተውጣጡ ብሪታኒያውያን ጋዜጠኞች ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል መባሉን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

#Russia #Britain #Sanction

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.