ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡
በዛሬው ዕለት እየተመረቁ ያሉ ተማሪዎች 574 ሲሆኑ÷ ከዚህ ውስጥ 60ዎቹ በድኅረ ምረቃ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
514ቱ ደግሞ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች ናቸው፡፡
በ2009 ዓ.ም የተመሰረተው ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ÷ ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ ዛሬ ለ4ኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
በምረቃ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ተመራቂዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!