Fana: At a Speed of Life!

የስልክ መስመሮችን ከቴሌ እውቅና ውጪ በመጠቀም የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕገወጥ የስልክ መስመሮችን ከቴሌ እውቅና ውጪ ሲጠቀም ነበር በሚል የተጠረጠረ ግለሰብ ከነ እቃው በቁጥጥር ስር መዋሉን የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ዘርፍ አስታወቀ።

በሐረሪ ክልል ድሬ ጠያራ ወረዳ ውስጥ አንድ ግለሰብ በሕገወጥ መንገድ የስልክ መስመር ቴክኖሎጂ በመጠቀም ወደ ውጪ ሀገር ሲያስደወል እንደነበር የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጃቢር አሊዪ ገልጸዋል።

በሕገወጥ መንገድ አገልግሎት ይስጥ የነበረው የስልክ መስመር የመንግስት ገቢን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳና በቴሌ አገልግሎት ላይ ኪሳራን የሚያስከትል እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡

በዚህም ግለሰቡ በድብቅ ግለሰቦችን ወደ ውጪ ሀገር በከፍተኛ ገንዘብ በማስደወል የግል ጥቅሙን በህገወጥ መንገድ ያገኝበት እንደነበርም ምክትል ኮማሽነሩ ተናግረዋል፡፡

በሕገወጥ መንገድ ወደ ሀገር የገባ ባለ አንቴና የስልክ ማሽን፣ ላፕቶፖች፣ ብዛት ያላቸው ሲም ካርዶች፣ ሞባይሎች፣ የዋይፋይ ሳጥኖች፣ የተለያዪ ኬብሎች፣ ፍላሾችና አንቴና በኤግዚቢት መያዛቸውም ነው የተገለጸው።

በዚህ ጉዳይ የተጠረጠረው ግለሰብ ላይም ምርመራ እንደተጀመረ ኃላፊው መግለጻቸውን ከሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.