በአቃቂ የገበያ ማዕከል በተከሰተ የእሳት አደጋ 16 የንግድ ሱቆች ተቃጠሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት 3 ሠዓት ከ10 ደቂቃ ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አቃቂ የገበያ መዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ 16 የንግድ ሱቆች ሙሉ በሙሉና በከፊል ተቃጠሉ፡፡
እሳቱ ወደገበያ ማዕከሉ ተስፋፎቶ በሰውና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠርም አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ፣ ሁለት የውኃ ቦቴ እና 44 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መሠማራታቸው ተገልጿል፡፡