ከለውጡ ወዲህ የቤንች ብሔር ቋንቋና ባህል እንዲታወቅ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤንች ብሔር ቋንቋና ባህል እንዳይታወቅ ሲደረግ ቢቆይም ከለውጡ ወዲህ በርካታ አበረታች ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ ጸጋዬ ማሞ ገለጹ፡፡
የቤንች ብሔር ባህልና ቋንቋ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።
አቶ ጸጋዬ ማሞ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የቤንች ብሔር ቋንቋና ባህል እንዳይታወቅ ሲደረግ የቆዬ ቢሆንም ከለውጡ ወዲህ በርካታ አበረታች ሥራዎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡
ለረጅም ዓመት ተቋርጦ የቆየው የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫና ምስጋና በዓልን ዳግም በተደራጀ መንገድ ለማክበር እንቅስቃሴ መጀመሩም አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በዓሉን መሰረት ያደረገ የቤንች ብሔር የቋንቋና ባህል ፓናል ውይይት መደረጉም የብሔሩን ቋንቋና ባህል ይበልጥ ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡
የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና ባህልን ከፍ አድርጎ በማክበር በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ከወዲሁ እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
በተስፋዬ ምሬሳ