Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን ያለውን ግጭት ለማስቆም የሱዳን ህዝብ የሠላም ጥረቶች መሪና ባለቤት መሆን አለበት – አምባሳደር ምስጋኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ያለውን ግጭት ለማስቆም የሱዳን ህዝብ የሠላም ጥረቶች መሪና ባለቤት መሆን አለበት ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አስገነዘቡ።

አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ የሱዳን ሪፐብሊክ እጩ አምባሳደር ኤልዘይን ኢብራሂም ሁሴን ጋር በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ግጭት ለማስቆም የሱዳን ህዝብ የሠላም ጥረቶች መሪና ባለቤት መሆን አለበት የሚል ፅኑ እምነት እንዳላት አምባሳደር ምስጋኑ አስረድተዋል።

በሱዳን የተከሰተው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ኢትዮጵያ ጥረት ስታደርግ መቆየቷን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በራሳቸው ተነሳሽነት ለሱዳን ሠላም መስፈን ጥረት ማድረጋቸውን በማንሳትም፤ ይህ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የሱዳን ስደተኞች ተገቢውን ጥበቃና ድጋፍ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይም መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.