የ #ጽዱኢትዮጵያ አካል የሆነ የጽዳት ሥራ በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተካሄደ
እንደ ሀገር ጽዱ አካባቢና ጽዱ የጤና ተቋማትን ለመፍጠር በተያዘው ዕቅድ መሰረት ሆስፒታሉ ለሠራተኞችና ለተገልጋዮች የሥራ ቦታን ውብ ለማድረግ የጽዳት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የጽዳት ሥራም የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 እና የሆስፒታሉ አመራሮች እና ሠራተኞች መሳተፋቸውን የሆስፒታሉ መረጃ አመላክቷል፡፡