Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ የክረምት የትራፊክ በጎ ፈቃድ አገልግሎትን አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን 6 ሺህ 500 በጎ ፈቃደኞች የሚሰማሩበት የክረምት የትራፊክ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዛሬ አስጀምሯል።

አዲስ አበባ ከተማን የበጎ ፈቃደኞች ከተማ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ በጎ ፈቃደኞች እያደረጉት ያለውን ንቁ ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ተጠይቋል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለከተማዋ ሁለንተናዊ ብልጽግና የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑም በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 15 ፕሮግራሞች የተካተቱበት መርሐ ግብር እየተከናወነ እንደሆነ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በመዲናዋ 6 ሺህ 500 በጎ ፈቃደኞች የሚሰማሩበት የክረምት የትራፊክ በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ130 አደባባዮች እንደሚከናወንም ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.