Fana: At a Speed of Life!

ሰላም ሚኒስቴርና ስተርሊንግ ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላም ሚኒስቴር እና በአሜሪካ የሚገኘው ስተርሊንግ ፋውንዴሽን ተጨማሪ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ሰፋፊ ሥራዎችን ለማከናወን የጋራ መግባባት ላይ ደረሱ፡፡

ሚኒስቴሩ ከስተርሊነግ ፋውንዴሽን ጋር በሰላም ግንባታ ሥራዎች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል፡፡

ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊት በሰጠው ድጋፍ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለተደረጉ የሰላም ግንባታ ሥራዎች በጎ አስተዋጽኦ ማበርከቱን በሚኒስቴሩ የሰላም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አወቀ አጥናፉ (ዶ/ር) አብራርተዋል፡፡

ስተርሊንግ ፋውንዴሽንን ወክለው የተገኙት የልዕኩ አባላት በበኩላቸው÷ ሚኒስቴሩ ሰላምን ለማረጋገጥ እየሠራ ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡

በቀጣይም ተጨማሪ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ሰፋፊ ሥራዎችን ለመሥራት የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.