የሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች በደገሃቡር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ተጠሪ ተቋማቱ እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በሶማሌ ክልል ደገሃቡር ከተማ የሕዝብ ፓርክ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ።
በችግኝ ተከላው ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌን(ዶ/ር) ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የጎሳ መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ ከችግኝ ተከላው በኋላ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ሥራ ማስጀመራቸውና ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ሚኒስቴሩ በጅግጅጋ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን የንግድ ዘርፍ ጉባዔ “ከሌብነት የፀዳ የንግድ ተቋም እንፍጠር” በሚል ስምምነት ማጠናቀቁ ይታወቃል፡፡