Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በብሪክስ የወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና በሩሲያ ኡሊያኖስክ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የብሪክስ ወጣቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እየተሳተፉ ነው፡፡

ምክር ቤቱ በትምህርት፣ ስልጠናና አቅም ግንባታ፣ ስራ ፈጠራ፣ ሣይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፣ በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በጤናና ስፖርት ዘርፍ በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ሊኖር ስለሚገባው የትብብር ማዕቀፍ እየመከረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስብሰባው እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.