Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ ፖሊሲ፣ ምዘናና ክፍያ ተማሪ እንደሚቀበል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ እራስ ገዝ እንደሚሆን እና በራሱ ፖሊሲ፣ መስፈርት፣ የምዘናና የክፍያ ሥርዓት ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ”ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሰቲ ለመደንገግ በወጣ” አዋጅ ቁጥር 1294/2015 እንዲሁም በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 537/2016 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ነው በራሱ ፖሊሲና መስፈርት መሠረት ወደ ሥራ እንደሚገባ የገለጸው፡፡

በዚህም መሠረት በ2017 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በርቀት በቅድመ ምረቃና በድኅረ ምረቃ መርሐ-ግብሮች የመማር ማስተማር ሥራውን በራስ ገዝነቱ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.