በሲስተም ማሻሻያ ሥራ ምክንያት ዛሬና ነገ የኃይል መቋረጥ ይኖራል- ማዕከሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላ ኢትዮጵያ እየተከናወነ በሚገኘው የሲስተም ማሻሻያ ሥራ ምክንያት ዛሬ እና ነገ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የኃይል መቋረጥ ሊከሰት እንደሚችል ተመላከተ፡፡
በማሻሻያው ምክንያት በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የኃይል ጭነት በሚበዛባቸው ሰዓታት ዛሬና ነገ የኃይል መቋረጥ ሊያጋጥም እንደሚችል የብሔራዊ ኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታውቋል፡፡
በመሆኑም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች ሥራው እስከሚጠናቀቅ ድረስ በትግዕስት እንዲጠብቁና ሌሎች ጊዜያዊ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል።