Fana: At a Speed of Life!

የሕዝባችንን ዘላቂ ሰላም ለማሻገር መሥራት ይጠበቅብናል – አቶ ደሳለኝ ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው በጀት ዓመት እንደ አመራር በአንድነት የሕዝባችንን ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለማሻገር መሥራት ይጠበቅብናል ሲሉ በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው አስገነዘቡ፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።

አቶ ደሳለኝ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በ2017 የማክሮ ኢኮኖሚ እድገትን ለማሳካት እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ብሎም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ልንረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡

ለዚህም ፈተናን በፅናት የሚሻገር፣ የቀጣዩን እጣ ፈንታ የሚወስን፣ የልማት ትሩፋቶችን እውን የሚያደርግና ሕዝብን ለማሻገር ኃላፊነቱን የሚወጣ አመራር ያስፈልጋል ማለታቸውን የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት እየተንከባለሉ የመጡና ያደሩ የልማት፣ የሰላምና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን አጠናክሮና አቀናጅቶ መፈፀም እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.