ሚኒስትሩ በጂቡቲ የሚኖሩ ዜጎችን ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚሠራ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በጂቡቲ ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም በጂቡቲ ሊገነባ ስለታቀደው የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት ድጋፍ፣ ስለ ዜጎች መብት፣ ስለ ሀገራዊ ጥሪዎች እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የኮሚዩኒቲ ተወካዮች ሐሳብ አንስተዋል።
ሚንስትሩ በበኩላቸው ኮሚዩኒቲው እስከ አሁን ለሀገራዊ ጥሪዎች ሲያደርግ ለነበረው ንቁ ተሳትፎ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
ይህ በጎ ተግባርም በይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማስገንዘባቸውን የኤምባሲው መረጃ አመላክቷል፡፡
የትምህርት ቤት ግንባታውን ለመደገፍ ከተዋቀረው ዐቢይ ኮሚቴ ጋር እንደሚሠሩ እንዲሁም በጂቡቲ ያሉ ዜጎችን ጥያቄዎች ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚወያዩ አስታውቀዋል፡፡