የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የልማትና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡
በክልሉ የተከናወኑ የልማት እና መልካም አሥተዳደር ሥራዎች አፈጻጸም ተገምግሟል፡፡
አቶ አሻድሊ በግምገማው ላይ እንዳሉት፤ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በልማት፣ በፖለቲካ እና በመልካም አሥተዳደር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በይበልጥ ለማጠናከር እየተሠራ ነው።
አመራሮች ወደ ሕዝቡ ወርደው ባደረጉት ድጋፍና ክትትል የተለዩ ክፍተቶችን ለመመለስ ያለመ አቅጣጫም በመድረኩ ላይ መቀመጡን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡