በክልሉ ማሕበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎትን ለማጠናከር እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሕብረተሰቡ ማሕበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎት ከመደበኛ የፍትሕ አገልግሎት ጋር በአማራጭነት እንዲያገኝ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ እሸቱ ጎዴቶ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ ከባድና ውስብስብ በሆኑ የሕግ ጉዳዮች በማሕበረሰቡ መካከል ዘላቂ ሰላምና አብሮነትን ለማምጣት በሚያስችል መልኩ የአካባቢ ባህልን መሰረት ባደረጉ ዕውቀቶች እልባት እያገኙ ናቸው፡፡
ሕብረተሰብን መሰረት ያደረገ የፍትሕ አገልግሎት የሕግ መሰረት ኖሮት በተደራጀ መንገድ በአማራጭነት አገልግሎት ላይ እንዲውል በተሰሩ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህም የባሕላዊ ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ በክልሉ ምክር ቤት መጽደቁን ጠቅሰው÷ የባሕላዊ ዳኝነት ሥርዓቱን የማደራጀት እና እውቅና የመስጠት ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
በክልሉ ሀሉም ቀበሌዎች የባሕላዊ ዳኝነት አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የማቋቋም እና አገልግልት ሰጪ ዳኞችን የመመልመል ሥራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
የፍትሕ አገልግሎትን ለሕብረተሰቡ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ አለማድረግ ከዘርፉ ተቋማት አሁናዊ ክፍተቶች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን ያነሱት አቶ እሸቱ÷ ክፍተቶቹን ለመሸፈን ማህበረሰብ አቀፍ ፍትህ አገልግሎትን ማጠናከር መፍትሔ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!