በሲዳማ ክልል ከ1 ሺህ 200 ቶን በላይ ሐር ተመረተ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል የእንስሳት ሃብት ልማት ቢሮ በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት 1 ሺህ 200 ቶን የሐር ምርት ተመርቷል አለ።
የቢሮው ም/ሃላፊ አደገ አየለ (ዶ/ር) ÷ በክልሉ በሚገኙ 13 ወረዳዎች የሐር ትል ልማት መጀመሩንና ጥሩ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን ተናግረዋል።
እስካሁን ምርቱ በአርባምጭ፣ አዲስ አበባና ሀዋሳ ለገበያ መቅረቡን ጠቁመው÷ በቀጣይ የገበያ ትስስሩን ለማስፋፋት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
ምርቱ በጥሬ ሲሸጥ እና ወደ ክር ሲቀየር ዋጋው የተለያየ በመሆኑ የአርሶ አደሮችን ገቢ ለማሻሻል ማሽን የማዳረስ ሥራ እንደሚሰራም አመልክተዋል፡፡
በሐር ትል ልማት ላይ የተሰማሩት የክልሉ ሴት አርሶ አደሮች በበኩላቸው ÷ በ2017 በጀት ዓመት የሐር ትል ማምረት ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ ይበልጥ ስኬታማ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በደብሪቱ በዛብህ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!