በ24 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የተገነባው የቦንጋ ከተማ አረንጓዴ ፓርክ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቦንጋ ከተማ የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የአረንጓዴ ፓርክ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋገሾ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የቦንጋ ከተማ እያከናወነ ያለው የከተማ ኮሪደር ልማት ሥራ በክልሉ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው።
የአረንጓዴ ፓርኩ ለአገልግሎት መብቃት የከተማ አስተዳደሩ በተሻለ አፈጻጸም እያከናወነ ለሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አንስተዋል።
ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና ጥራት እንዲጠናቀቁ ክትትል፣ ቁጥጥር እና ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለውም ጠቁመዋል።
የአረንጓዴ ፓርኩ በቀጣዮቹ ቀናት በተሟላ መልኩ ለሕዝብ አግልግሎት እንደሚሰጥ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ኢዮብ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
ፓርኩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አስተባባሪነት በ24 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ መገንባቱን አስረድተዋል።
ፓርኩ በውስጡ መናፈሻ፣ የህጻናት መጫወቻ፣ የካፌ አገልግሎት እንዲሁም በፓርኩ ዙሪያ ጌጠኛ የእግረኛ መንገድ እና የመኪና ማቆሚያ ያካተተ መሆኑን አንስተዋል።
በመርሐ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!