ፈተናዎችን በመቋቋም በሁሉም ዘርፎች ስኬቶች ተመዝግበዋል – ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በመቋቋም በሁሉም ዘርፎች ስኬቶች አስመዝግባለች አሉ።
ሚኒስትሩ የ2017 በጀት ዓመት አበይት የመንግስት ክንውኖችን እንዲሁም የሚቀጥለው ዓመት ተስፋዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ሀገራችን ውስጣዊ እና ውጫዊ ፈተናዎችን ተቋቁማ በጽናት ኖራለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለእነዚህ ችግሮች ባለመሸነፍ ክብር እና ነጻነት የሚገኘው በጽናት መሆኑን ለዓለም አሳይታለች ነው ያሉት።
ፈተናዎችን በመቋቋም በሁሉም ዘርፎች ስኬቶች መመዝገባቸውን አንስተው፤ ለመጪው ትውልድ ጠንካራ እና የጸናች ሀገር የማስተላለፍ ኃላፊነት አለብን ሲሉ አስገንዝበዋል።
ጽናት ለሀገር የሚከፈል የክብር አርማ መሆኑን በመግለጽ፤ ጽናት ያለው ትውልድ ሀገር ይገነባል፤ ይጠብቃል፤ ያሻግራል ብለዋል።
ታሪክ የሚያስተምረን ያለ መስዋዕትነት ያደገ ሀገር አለመኖሩ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያም ችግሮችን ተቋቁማ ታሪኳን በደማቅ የጽናት ቀለም መጻፏን አስረድተዋል።
በጋራ ጀግንነት ሀገራችንን አስከብረን ሰንደቅ ዓላማችንን አኑረናል ያሉት ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፤ በጽናት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከግብ ደርሷል ብለዋል።
በዘንድሮ ክረምት 714 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምበር መተከሉን አንስተው፤ ይህ ሁሉ የአብሮነት ጽናታችንን የሚያሳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!