Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማንነታችንና ብሔራዊ አርማችን ነው – የግድቡ ሠራተኞች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማንነታችን እና ብሔራዊ አርማችን ነው አሉ በሕዳሴ ግድብ በተለያዩ ሙያዎች የተሰማሩ ሠራተኞች፡፡
ያለፉት 14 ዓመታትን በሕዳሴ ግድብ ቴክኒሻን ሆነው ያገለገሉት አቶ ሰለሞን ያረጋል÷ ለሀገር ልማትና እድገት የተከፈለው መስዋዕትነት ፍሬ በማፍራቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
ግድቡ ውስብስብ ችግሮችን አልፎ ለዚህ በመብቃቱና የታሪኩ አካል በመሆናቸው ኩራት እንደሚሰማቸውም ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡
በሕዳሴ ግድብ 13 እና 7 ዓመታትን ያገለገሉት በየነ ሆዴ እና አስማማው ጌታቸው በበኩላቸው ÷ የበረሃውን ንዳድ ተቋቁመው የኢትዮጵያን አደራ በስኬት በመወጣታቸው መደሰታቸውን ይናገራሉ፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ኢትዮጵያዊነት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች እንደሆኑም አንስተዋል።
አንድ ስንሆን ሁሉንም ማሸነፍ እንችላለን ያሉት ሠራተኞቹ ÷ ግድቡ የሕልውና እና የአሸናፊነት ተምሳሌት ነው ብለዋል፡፡
የሕዳሴ ግድብን በጋራ እንዳሳካነው ሁሉ በቀጣይ ለሚተገበሩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች በጋራ ልንቆም ይገባል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በአልማዝ መኮንን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.