Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የ500 ሚሊየን ብር ብድር ሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የ500 ሚሊየን ብር ብድር ሰጠ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ብድሩ በአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም በኩል የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ብድሩ በዋነኝነት ለግብርና እና ለፋብሪካ ምርቶች የሚውል መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ አዳነች የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
አስተዳደሩ በምክትል ከንቲባ የሚመራ ግብረ ሃይል አቋቁሞም የኑሮ ውድነቱን ምክንያት እና መፍትሄውን ማስጠናቱ የተገለፀ ሲሆን በጥናቱም በዋናነት የኑሮ ውድነቱ ምክንያት የገቢያ አሻጥር መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
ሌላው ደግሞ የተመረተው ምርት ወደ ገበያ እንዳይገባ ሲሰራ መቆየቱ እና የምርት እጥረት መኖሩ ነው ተብሏል፡፡
ይህንንም የሚያደርገው በኢኮኖሚ ዘርፍ ጉልበት ያካበቱና በፖለቲካ ኪሳራ የደረሰባቸው ናቸው የተባለ ሲሆን ህብረተሰቡ መንግስት ላይ እንዲማረር ታስቦ የተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል ምክትል ከንቲባዋ፡፡
በዚህም አሁን ከተማ አስተዳደሩ ምርት እንዲጨምር ለአምራቹ ሁኔታዎች እንዲመቻቹለት እና ህብረት ስራ ማህበራት በቀጥታ ምርቶቹን ወደ ህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ ለሸማች ህብረት ሰራ ማህበራት የ500 ሚሊየን ብር ብድር ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ገበያ ላይ ያለውን ቁጥጥር ለማስፋት በማሰብ በ200 ሺህ መጋዘኖች ላይ ብርበራ ተደርጎ 30 ሺህ ያህሉ ላይ ምርት አከማችተው በመገኘታቸው ርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡
2 ሺህ 800 ሚዛን ቤቶችም ሚዛን ሲያዛቡ ተገኝተው ርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ ኑሮን ለማረጋጋት የተለያዩ ርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.