አንደኛው የሀገር አቀፍ የባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ሲምፖዚየም ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር አዘጋጅነት የአንደኛው የሀገር አቀፍ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ሲምፖዚየም “ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል።
የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ሲምፖዚየሙን በይፋ ከፍተዋል።
አፈጉባኤው በንግግራቸው “ባህል፣ ስፖርትና ቱሪዝምና ከችግሮቻችን መውጫ መንገዶቻችን ናቸው” ሲሉ የሲምፖዚየሙን አስፈላጊነት በአፅኖት ገልፀዋል።
በሲምፖዚየሙ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ዝግጅቱን የተለያዩ የፌደራልና የክልል አመራሮች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የዩንቨርሲቲ ተወካዮችና ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!