በመዲናዋ ነገ አዲስ አስተዳደር ይመሠረታል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ የአዲስ አበባ ከተማ አዲስ አስተዳደር ይመሠርታል፡፡
በዚሁ መሠረት መስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም በመዲናዋ የህዝብ ይሁንታ ያገኘው አዲሱ መግሥት እንደሚመሠረት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የከተማዋ አስተዳደር ምክር ቤት ነገ በሚያካሂደው የምስረታ ጉባኤው፣ አፈጉባኤውን እና ምክትል አፈጉባኤውን ይመርጣል፡፡
138 አባላት ያሉት ምክር ቤቱ በዕለቱ አዳዲስ የካቢኔ አባላትን የሚሰይም ሲሆን÷ የቋሚ ኮሚቴ አባላትንም ይመርጣል፡፡
በተጨማሪም ልዩ ልዩ የአስተዳደር እና የአደረጃጀት ደንቦችን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!